የኤፍራጥስ ወንዝ እና ሌሎች መጣጥፎች / Nejlevnější knihy
የኤፍራጥስ ወንዝ እና ሌሎች መጣጥፎች

Kód: 51328508

የኤፍራጥስ ወንዝ እና ሌሎች መጣጥፎች

Autor Deacon Henok Haile

ወደ እርስዋ ቀርቦ ውኃ አጠጪኝ አላት፤ አባ ጊዮርጊስ "አንተ የሕይወት ውኃ ስትሆን ከሳምራዊትዋ ሴት ውኃን ለመንህ" እንዳለ የሕይወት ውኃ ክርስቶስ ውኃ ለመናት፡፡ እርሱ የተጠማው ውኃ ሳይሆን የእርስዋን ነፍስ ነበረ፡፡ እርስዋም አንተ አይሁዳዊ ስትሆን ሳምራዊት ከምሆን ከእኔ ውኃ ትለምናለህ? አለችው፡፡ እንዲህ ነው ነገሩ፡፡ የቆሰለች ነፍስ ስለ ዘር ታወራለች፡፡ ... celý popis

442


Skladem u dodavatele
Odesíláme za 14-21 dnů
Přidat mezi přání

Mohlo by se vám také líbit

Dárkový poukaz: Radost zaručena

Objednat dárkový poukazVíce informací

Více informací o knize የኤፍራጥስ ወንዝ እና ሌሎች መጣጥፎች

Nákupem získáte 44 bodů

Anotace knihy

ወደ እርስዋ ቀርቦ ውኃ አጠጪኝ አላት፤ አባ ጊዮርጊስ "አንተ የሕይወት ውኃ ስትሆን ከሳምራዊትዋ ሴት ውኃን ለመንህ" እንዳለ የሕይወት ውኃ ክርስቶስ ውኃ ለመናት፡፡ እርሱ የተጠማው ውኃ ሳይሆን የእርስዋን ነፍስ ነበረ፡፡ እርስዋም አንተ አይሁዳዊ ስትሆን ሳምራዊት ከምሆን ከእኔ ውኃ ትለምናለህ? አለችው፡፡ እንዲህ ነው ነገሩ፡፡ የቆሰለች ነፍስ ስለ ዘር ታወራለች፡፡ ተስፋ የቆረጠች ነፍስ የዘር ጉዳይ ሲሆን ልሳንዋ ይከፈታል፡፡ ውኃ ለማጠጣት ዘር መጠየቅን ምን አመጣው፡፡ ውኃው አይሁዳዊ ነው? ወይንስ ሳምራዊ? ውኃ ጠማኝ የሚል ሁሉ ውኃ ይገባዋል እንጂ ዘሩ አይጠየቅም፡፡ እርስዋ ግን ጠየቀችው፡፡ በእርግጥ ይህች ሳምራዊት ሴት ይህን ጥያቄ የጠየቀችው ክርስቶስ መሆኑን ከማወቅዋ በፊት ነበር፡፡ክርስቶስ መሆኑን ካወቀች በኋላ ግን ስለ አይሁዳዊነትና ስለ ሳምራዊነት ስትናገር አልተሰማችም፡፡ "አንተ አማራ ስትሆን ጉራጌ ከምሆን ከእኔ ውኃ ለምን ትለምናለህ?" "አንቺ ኦሮሞ ስትሆኚ ትግሬ ከምሆን ከእኔ እንዴት ውኃ ትለምኛለሽ?" በሚል ጥያቄ ሀገሩን ያጨናነቁተ ክርስቶስን ያወቁ ክርስቲያኖች መሆናቸው ግን ልብን የሚሰብር እውነታ ነው፡፡ በዚህ ጠባያችን እንደ ክርስቲያን ሳንኖር እንደ ክርስቲያን ልንሞት መሆኑ ምንኛ ያሳዝናል?

/ከውስጥ ገጽ የተወሰደ/

ይህ መጽሐፍ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ያዘጋጃቸው ልዩ ልዩ መጣጥፎችን ይዟል፡፡

ክፍል አንድ

ልዩ ልዪ ስብከቶች

የኤፍራጥስ ወንዝ /6/፣ እግዚአብሔር እንዴት ይፈርዳል? /21/፣ የካም ትውልድ /31/፣ ደስ ይበላችሁ /42/፣ ጌታ ሆይ ይህን ውኃ ሥጠኝ /49/፣ በገነት ያሉ ሦስት አስደናቂ ነገሮች /54/፣ ጌታ ሆይ እኔ እሆንን? /55/፣ የትሕትና ትምህርት ቤት /58/፣ እንዴት ወድቀን እንዴት ተነሣን? /66/፣ ሁለቱ መታጠቢያዎች /71/፣ ለማንም እንዳትናገር /74/፣ አባቶቻችን እንዲህ እንዲህ አሉ /79/፣ በሰንበት መፍረስ /91/፣ ዛሬ ነገ ነው? /93/፣ መርጦ መወለድ /96/፣ ኮሜድያኑ ሰማዕት /98/፣ ባለጸጋ ነዳያን /99/፣ ስሞት ዓይኔን የሚከድንልኝ ማን ይሆን? /105/፣ የግርፊያ ሰልፍ /110/፣ ምግብ እንዲገዙ ሕዝቡን አሰናብታቸው /117/፣ ቤተ ክርስቲያንና ሚሽነሪዎች /121/

ክፍል ሁለት

የበዓላት ስብከቶች

ዘልደት

የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? /126/

ዘጥምቀት

መጥምቁ ዮሐንስን ማን አጠመቀው?/131/

ታኅሣሥ ገብርኤል

ከክርስቶስ በፊት የነበሩ ክርስቲያኖች /140/

ጾመ ነነዌ

ጣዕም የሌለው ስብከት /151/

ዘኒቆዲሞስ

በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጣ /158/

ዘሆሳዕና

ንጉሥ በአህያ ላይ /161/፣

የትንሣኤ ስብከቶች፣

፩ አትክልተኛ መስሏት ነበር /164/፣ ፪ ከሁሉ በኋላ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ታየኝ /171/፣ ፫ ፍቅር ቁስል ነው /178/

ዘጰራቅሊጦስ

የግንቦት ልደታ

የደብረ ታቦር ስብከቶች

Parametry knihy

442

Oblíbené z jiného soudku



Osobní odběr Praha, Brno a 46010 dalších

Copyright ©2008-26 nejlevnejsi-knihy.cz Všechna práva vyhrazenaSoukromíCookies


Můj účet: Přihlásit se
Všechny knihy světa na jednom místě. Navíc za skvělé ceny.

Nákupní košík ( prázdný )

Vyzvednutí v Balikovně a PPL
boxech
zdarma nad 1 499 Kč.

Nacházíte se: